በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምሥራቅ ሸዋ የአርቱ ቅድስት አርሴማ ደብር ሁለት አገልጋዮች በታጣቂዎች እንደተገደሉ ሀገረ ስብከቱ ገለጸ

በምሥራቅ ሸዋ የአርቱ ቅድስት አርሴማ ደብር ሁለት አገልጋዮች በታጣቂዎች እንደተገደሉ ሀገረ ስብከቱ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:44 0:00

በምሥራቅ ሸዋ የአርቱ ቅድስት አርሴማ ደብር ሁለት አገልጋዮች በታጣቂዎች እንደተገደሉ ሀገረ ስብከቱ ገለጸ

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን፣ በአዳማ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው የአርቱ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች እንደተገደሉ፣ የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ገለጸ፡፡

ግድያው “ያልታወቁ” ባሏቸው ታጣቂዎች፣ ከትላንት በስቲያ እንደተፈጸመ፣ ለአሜሪካ ድምፅ የገለጹት የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ልዩ ጽሕፈት ቤት ሓላፊ መጋቤ ጥበባት ጌቱ ሞቲ፣ በታጣቂዎቹ ታግተው የተወሰዱ አገልጋዮችም መኖራቸውን አመልክተዋል፡፡

በወረዳው የሚገኘውን የቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በአንድነት የሚመራው የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ አባ ገብረ ጻድቅም፣ ጥቃቱ ለሌሊቱ ጸሎተ ሰዓታት እና ማኅሌት በተዘጋጁ አገልጋዮች ላይ እንደተፈጸመ ገልጸዋል። ስለጉዳዩ፣ ከአዳማ ከተማ አስተዳደር እና ከኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG