በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዐማራ ክልል ሁለት ሚሊዮን ሕዝብ አስቸኳይ ርዳታ ይፈልጋል - ክልሉ


በዐማራ ክልል ሁለት ሚሊዮን ሕዝብ አስቸኳይ ርዳታ ይፈልጋል - ክልሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:22 0:00

በዐማራ ክልል ሁለት ሚሊዮን ሕዝብ አስቸኳይ ርዳታ ይፈልጋል - ክልሉ

በዐማራ ክልል በልዩ ልዩ ዞኖች በተከሠተው ድርቅ ለተጎዱና ከተለያዩ ዞኖች ለተፈናቀሉ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ዜጎች፣ አስቸኳይ የዕለት እህል ርዳታ እንዲቀርብ ጥሪ ተላለፈ፡፡

የዐማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋሁን ባያብል፣ ዛሬ ረቡዕ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በክልሉ አብዛኛው ቆላማ አካባቢዎች ድርቅ ተከሥቷል፡፡

ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ፣ ጊዜ የማይሰጥ አስቸኳይ የዕለት ምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልገው የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ ከእኒኽም ውስጥ በግጭት ምክንያት፣ ከአገሪቱ ልዩ ልዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በካምፕ እና ከማኅበረሰቡ ጋራ ተቀላቅለው የሚኖሩ እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል።

በክልሉ፣ በሰው ሠራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ የተከሠተውን የምግብ እጥረት ለማቃለል፣ መንግሥት ጥቂት ጥረት ቢያደርግም፣ የጸጥታ ችግሩ የሰብአዊ ርዳታን ለማጓጓዝ ዕንቅፋት እንደፈጠረባቸው፣ ዲያቆን ተስፋሁን ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አያይዘውም፣ በውጭ እና በሀገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ለጋሽ ድርጅቶች፣ የርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG