በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፈ-ጉባዔማካርቲ በፓርቲያቸው አባል ከስልጣን እንዲነሱ ጥያቄ ቀረበ


አፈ-ጉባዔ ኬቪን ማካርቲ
አፈ-ጉባዔ ኬቪን ማካርቲ

በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ከሪፐብሊካን ፓርቲው ወገን የሆኑት ማት ጌት፡ አፈ-ጉባዔ ኬቪን ማካርቲ ከስልጣን ይነሱ ዘንድ ምክር ቤቱ ድምፅ እንዲሰጥ የሚያስገድድ ጥያቄ አቅርበዋል።

ጌትስ የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በቀጣዮቹ ቀናት እንዲካሄድ ለማድረግ በማቀድ ትላንት ሰኞ ነው ‘ከስልጣን የማስነሳቱን’ ጥያቄ ያቀረቡት።

ማካርቲ፡ ኤክስ በተሰኘው የማሕበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ “ያምጡት” ሲሉ የጌትስ ጥያቄ እንደማያሳስባቸው በሚያሳይ አቀራረብ ውድቅ አድርገውታል።

ጌትስ፡ ማካርቲን ከስልጣን ለማስነሳት 435 መቀመጫዎች ካሉት ምክር ቤት የአብላጫ ድምጽያስፈልጋቸዋል። የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት በምክር ቤቱ 221 መቀመጫዎችን ሲቆጣጠሩ፤ በአነስተኛ ቁጥር የሚበለጡት የዲሞክራት ፓርቲው አባላት ደግሞ 212 መቀመጫዎች አሏቸው።

ጌትስ በማካርቲ ላይ ያቀረቡት ‘ከስልጣን ይነሱ’ ጥያቄ የፌድራልመንግስቱን እንዳይዘጋ ያደረገው ለአጭር ጊዜ የሚውል የመንግስት በጀት እንዲጸድቅ መሰንበቻውን በምክር ቤቱ በተሰጠው ድምጽ ማካርቲ ‘የተቀናቃኙን የዲሞክራት ፓርቲ አባላት ድጋፍ ተጠቅመዋል’ የሚል ነው።

ማካርቲ ባለፈው የጥር ወር ለምክር ቤቱ አፈ ጉባኤነት ስልጣን የበቁት ጌትስ እና የሪፐብሊካን ፓርቲያቸው እጩ እንዳይሆኑ የተቃወሙ ሌሎችየምክር ቤቱ አባላት የደቀኑባቸውን ፈተና ለማለፍ በተደጋጋሚ ዙር ከተካሄደ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት በኋላ ነው። ማካርቲ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ለመጠየቅ ለፈለገ ማንኛውም የምክር ቤቱ አባል ድምጽየሰሚሰጥበትን መድረክ ለመፍቀድ ከተስማሙ በኋላ ነበር።

በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ከዚህ ቀደም አንድም የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ከኃላፊነቱ ተነስቶ አያውቅም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG