በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተር 99ኛ የልደት ቀናቸውን አከበሩ


ፋይል - የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተር
ፋይል - የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተር

በጠና ታመው ሆስፒታል ከገቡ ሰባት ወራትን ያስቆጠሩት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተር፣ በማይድን በሽታ ለሚሰቃዩ ሰዎች የሚሰጥ የመጨረሻ ደረጃ እንክብካቤ እየተደረገላቸው በሚገኙበት ወቅት 99ኛ ዓመት የልደት በዓላቸው ተከብሮላቸዋል።

የቀድሞ ፕሬዝዳንቱ እና ባለቤታቸው ሮዛሊን፣ በጆርጂያ ግዛት የትውልድ ከተማቸው ውስጥ በተካሄደው የኦቾሎኒ ፌስቲቫል ላይ በድንገት መታየታቸውም ተገልጿል።

"ሆስፒስ ስለተሰኘው የህክምና አሰጣጥ የተሳሳተ ግንዛቤ ያለ ይመስለኛል ምክንያቱም ሰዎች ለመሞት ቀናት ለቀራቸው ሰዎች ብቻ የሚሰጥ ይመስላቸዋል" ያሉት የጂሚ ካርተርን የህይወት ታሪክ የፃፉት ደራሲ ጆናታን ኦልተር የካርተር ቤተሰቦች የመጨረሻውን የህይወታቸውን "እስከቻሉ ድረስ፣ በሚችሉትን መጠን፣ የሚችሉትን ያደርጋሉ" ብለዋል።

የቀድሞው ፕሬዝዳንት እ.አ.አ በ1982 ያቋቋሙት ካርተር ማዕከል የተሰኘው መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፔጅ አሌክሳንደር በበኩላቸው ፣ "መልካም ልደት ለመመኘት ሳነጋግራቸው "99 ዓመት መሙላት ምን ያክል ደስተኛ እንደሚያደርግ እርግጠኛ አይደለሁም" እንዳሏቸው በመግለፅ፣ ካርተር አሁን እንደቀድሞው አካላዊ ችሎታዎች ባይኖሯቸውም፣ አይምሯቸው ግን አሁም ፈጣን እንደሆነ ገልፀዋል።

ካርተር ስለሚደረግላቸው ድጋፍ እና አድናቆት እንደሚረዱ እና ዋጋ እንደሚሰጡት የገለፁት አሌክሳንደር፣ በተለይ በቪዲዮ እና በፎቶ አማካኝነት በካርተር ማዕከል በኩል በሚጎርፍላቸው የመልካም ልደት መግለጫ ደስተኛ እንደሆኑም አመልክተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG