በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማሊ ጦር ከሰሜን ተገንጣይ አማፂያን ጋር አዲስ ውሂያ መጀመሩን አስታወቀ


ቲምቡክቱ፣ ማሊ
ቲምቡክቱ፣ ማሊ

በማሊ ሰሜናዊው ክፍል፣ በጦር ኃይሎች እና በታጣቂዎች መካከል አዲስ ውጊያ መቀስቀሱን፣ የማሊ ጦር እሁድ እለት አስታውቋል። በችግር ውስጥ በምትገኘው የምዕራብ አፍሪካ ሀገር የጦር ኃይል ላይ በተከታታይ ከተፈፀሙ ጥቃቶች ውስጥ አንዱ መሆኑም ተገልጿል።

የጦር ኃይሉ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባወጣው መግለጫ፣ ተገንጣይ አማፂያኑ ተቆጣጥረናሉ ባሉት ባምባ የተሰኘ አካባቢ፣ እሁድ ጠዋት ከ"አሸባሪዎች" ጋር "ጠንካራ ውጊያ" አካሂደናል ብሏል።

አማፂያኑ ሰሜናዊውን አካባቢ እንደያዙ፣ የአዛውድ እንቅስቃሴዎች ቅንጅት (ሲማ) የሚመራው ቋሚ ስልታዊ ማዕቀፍን ወክለው በማህበራዊ ሚዲያ ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል።

'ሲማ' የራስ ገዝ አስተዳደርን ወይም ከማሊ ግዛት ነጻ መውጣትን የሚፈልጉ የቱዋሬግ ቡድኖች የሚበዙበት ጥምረት ነው። ጥመቱ ቅዳሜ እለት ባወጣው መግለጫ፣ በሀገሪቱ ማዕከላዊ ክፍል ባደረሰው ጥቃት በማሊ ጦር ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ማድረሱን እና 81 ወታደሮችን መግለፁን ግልጿል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG