በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን የአሜሪካን በጀት በፊርማቸው አፀደቁ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን

የአሜሪካ ምክር ቤት በበጀት ላይ ስምምነት ሊደርስ ባለመቻሉ የመንግስት ሥራ ሊቆም ከአንድ ሰዓት ያነሰ ጊዜ በቀረበት ወቅት፣ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እስከ ህዳር አጋማሽ ድረስ የሚያቆየውን ረቂቅ የበጀት ህግ በፊርማቸው በማፅደቅ የመንግስት ስራን ከመዘጋት ታድገዋል።

ባይደን፣ ቀደም ሲል ትዊተር በሚል ስሙ በሚታወቀው የአሁኑ ኤክስ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ፣ ላይ ረቂቅ ህጉን ሲፈርሙ የሚያሳይ ፎቶአቸውን ቅዳሜ እለት አጋርተዋል። አብረው ባስተላለፉት መልዕክትም፣ ምክርቤቱ ለጠቅላላው የበጀት ዓመት የተጠየቀውን ገንዘብ በአስቸኳይ እንዲያፀድቅ አሳስበዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) ባልተለመደ መልኩ ቅዳሜ ምሽት ባካሄደው ስብሰባ ረቂቅ ህጉን አሳልፎ ለመጨረሻው ፊርማ ወደ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመላኩ፣ ሊዘጋ በቋፍ ላይ የነበረው የፌደራል መንግስት ስራውን ቀጥሏል።

የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ከተጠናቀቀ በኃላ ባይደን ባወጡት መግለጫ፣ የሕጉ መፅደቅ "በሚሊየን የሚቆጠሩ ታታሪ አሜሪካውያን ሰራተኞች ላይ ተገቢ ያልሆነ ስቃይ ሊያስከትል ይችል የነበረ አላስፈላጊ ቀውስን ተከላክሏል" ብለዋል።

የበጀት ህጉ ባይፀድቅ፣ ከአራት ሚሊየን በላይ የአሜሪካ ወታደራዊ አገልግሎት ሰራተኞች እና ሌሎች የመንግስት ሰራተኞች ክፍያ እንደማያገኙ ተሰግቶ ነበር። ጡርተኞችም ወርሃዊ ክፍያቸውን የማያገኙ በመሆኑ አስቤዛ መግዛትም ሆነ ሌሎች ክፍያዎችን መፈፀም አይችሉም ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG