በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ሱዳን በተደራራቢ ግጭቶች፣ የአየር ቀውስ፣ ተላላፊ በሽታዎች እና ረሃብ እየተሰቃየች ነው - ተ.መ.ድ


ፋይል - በደቡብ ሱዳን፣ ጁባ ከተማ አቅራቢያ፣ የሱዳን ስደተኞችን በሚያስተናግደው ጎሮም የተሰኘ መጠለያ ጣቢያ፣ ሱዳናውያን ስደተኞች ውሃ ሲቀዱ ይታያሉ።
ፋይል - በደቡብ ሱዳን፣ ጁባ ከተማ አቅራቢያ፣ የሱዳን ስደተኞችን በሚያስተናግደው ጎሮም የተሰኘ መጠለያ ጣቢያ፣ ሱዳናውያን ስደተኞች ውሃ ሲቀዱ ይታያሉ።

በከፍተኛ ደረጃ እየተባባሰ የመጣው ከፍተኛ የምግብ እጥረት፣ አጣዳፊ ረሃብ እና እያሽቆለቆለ የሄደው የጤና ሁኔታ፣ በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎችን ደህንነት አደጋ ላይ መጣሉን፣ የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ። የአየር ንብረት ቀውሱ ሲጀምር ሁኔታው እየተባባሰ እንደሚሄድም ጨምሮ ገልጿል።

በዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ ቀንድ የሚደርሱ ክስተቶች አስተዳዳሪ የሆኑት ሊስቤት አልብሬኽት "ደቡብ ሱዳን ግጭት፣ የአየር ንብረት ቀውስ፣ የረሃብ ቀውስ እና የበሽታ ወረርሽኝ ለዓመታት ተደራርበው ሲከሰቱባት የኖረች ሀገር ነች" ብለዋል።

"በዚህ አመት ከአራት ደቡብ ሱዳናውያን ሦስቱ ሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል" ያሉት አልብሬኽት፣ እነዚህ ሦስቱ ሰዎች ለረሃብ የተጋለጡ መሆናቸውን እና ቁጥሩ እየተባባሰ እንደሚሄድ አብራርተዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው ሪፖርት፣ 6.3 ሚሊየን ደቡብ ሱዳናውያን በአስከፊ ረሃብ እየተሰቃዩ መሆናቸውን እና 12 ሚሊየን ከሚሆነው የሀገሪቱ ህዝብ፣ ከ9 ሚሊየን በላይ የሚሆኑት ኑሮዋቸው በሰብዓዊ እርዳታ የተመሰረተ መሆኑን ይፋ አድርጓል።

በዚህ ዓመት ብቻ ቢያንስ 150 ሺህ ህፃናት በከባድ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት ህክምና እንደተደረገላቸው ያብራሩት የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያዋ፣ ከፍተኛ የሙቀት መጨመር እና ከባድ ዝናብ የሚያስከትለው ኤል ኒኖ የተሰኘው የአየር ንብረት ክስተት በተቃረበበት ወቅት፣ በደቡብ ሱዳን ላይ የተጋረጠው ሰብዓዊ ቀውስ እየተባባሰ እንደሚሄድ አመልክተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG