በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት ኃይል የመውጣቱ ሂደት እንዲዘገይ አምስት ሀገራት ጠየቁ


ፎቶ ፋይል (flickr)
ፎቶ ፋይል (flickr)

በሶማሊያ ለሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ልዑክ ኃይል የሚያዋጡ ሀገራት፣ ሶማሊያ ልዑኩ ሀገሪቱን ለቆ የመውጣቱ ሂደት እንዲዘገይ ለጸጥታው ም/ቤት ያቀረበችውን ጥያቄ እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።

ኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ቡሩንዲ፣ ጅቡቲ፣ እና ኡጋንዳ በጋራ በመሆን፣ 3ሺሕ የልዑኩ ወታደሮችን በቅርቡ ከሶማሊያ ለማሰወጣት የተያዘው ዕቅድ እንዲዘገይ ለጸጥታው ም/ቤት ጥያቄ አቅርበዋል። አምስቱ ሀገራት ወታደሮቹን የማስወጣቱ ሂደት በ90 ቀናት እንዲዘገይ ጠይቀዋል።

በሶማሊያ ያለው የጸጥታ ሁኔታ አሁንም አሳሳቢ እንደሆነ እና፣ በተለይም በሚለቀቁት ወታደራዊ ሠፈሮች አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ሁኔታ አሳሳቢ ነው ሲሉ አምስቱ ሀገራት ባቀረቡት ጥያቄ ላይ ማመልከታቸው ታውቋል።

ሶማሊያም ለጸጥታው ም/ቤት ባስገባቸው ማመልከቻ ተመሳሳይ ስጋቷን ገልጻ ነበር።

በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት ኃይል እስከ 2024 መጨረሻ ድረስ ደረጃ በደረጃ ለቆ እንዲወጣ የጸጥታው ም/ቤት በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጀመሪያ ላይ ውሳኔ አሳልፎ ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG