ባለፈው ሰኞ፣ የሴቶች ማራቶን የዓለም የክብረ ወሰንን በማሻሻል የዓለም መነጋገርያ የኾነችው አትሌት ትዕግሥት አሰፋ፣ ዛሬ ወደ አገሯ ኢትዮጵያ ተመልሳለች።
የኢትዮጵያ አትሌትክስ ፌዴሬሽን አመራሮች እና ሌሎች ባለሥልጣናት፣ ለትዕግሥት እና የውድድር ልዑኩ አቀባባል አድርገውላቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ አትሌትክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፣ ትዕግሥት ያስመዘገበችው ድል፣ ዘንድሮ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ካስመዘገቡት ሁሉ ታላቁ ነው፤ ብላለች። ባለድሏ አትሌት ትዕግሥትም፣ በውጤቷ በጣም ደስተኛ እንደኾነችና ከአሁን በኋላ ለቀጣዩ ውድድር ከወዲሁ ዝግጅቷን እንደምትጀምር አስታውቃለች፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡
መድረክ / ፎረም