በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግሪክን ድጋሚ የመታው ዝናብና አውሎ ነፋስ ከባድ ጉዳት አደረሰ


በማዕከላዊ ግሪክ የጣለው፣ እስከዛሬ ተመዝግቦ የማያውቅ ከፍተኛ የዝናብ መጠን ያስከተለውን የጎርፍ አደጋ ተከትሎ፣ ይህ ግለሰብ ለዘመዱ መድሀኒት ለማድረስ በጎርፍ ውሃ ውስጥ ሲሄድ ይታያል።
በማዕከላዊ ግሪክ የጣለው፣ እስከዛሬ ተመዝግቦ የማያውቅ ከፍተኛ የዝናብ መጠን ያስከተለውን የጎርፍ አደጋ ተከትሎ፣ ይህ ግለሰብ ለዘመዱ መድሀኒት ለማድረስ በጎርፍ ውሃ ውስጥ ሲሄድ ይታያል።

ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ፣ ዛሬ ሐሙስ ግሪክን ለሁለተኛ ጊዜ የመታት ከባድ ዝናብና አውሎ ነፋስ በአንዳንድ የማዕከላዊ አገሪቱ ክፍሎች ከባድ ጉዳት አድርሷል፡፡

ኤልያስ ተብሎ የሚጠራው ከባድ ዝናብና አውሎ ነፋስ ያስከተለው የጎርፍ አደጋ መንገዶችን በመጠራረግ እና ድልዮችን በማፈራረስ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን አጥለቅልቋል፡፡

የከፋ ጉዳት የደረሰው በቮሎስ አካባቢ እና በአቅራቢያው በሚገኘው በኤቪያ ደሴት ሰሜናዊ ክፍል ላይ ነው፡፡

አካባቢው ከሁለት ዓመት በፊት በደረሰው ከፍተኛ የሰደድ እሳት ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ መሆኑን ባለስልጣናት ተናግረዋል።

የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች የነፍስ አድን ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት በማዕከላዊ ከተማ ቮሎስ በደረሰው ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአቅራቢያው በሚገኙ ተራራማ መንደሮች ውስጥ እንዲቆዩ ማድረጉንም ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

በዚህ ወር መጀመሪያ ተከስቶ የነበረው አስከፊ የአየር ሁኔታ በዚሁ አካባቢ አድርሶት በነበረው አደጋ 16 ሰዎች የሞቱ ሲሆን፣ በእርሻ እና በመሰረተ ልማት ላይ 2.3 ቢሊዮን የተገመተ ጉዳት ማድረሱ የሚታወስ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG