በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የሻራ ቀበሌ፣ የዘፈቀደ እስሩ እንደቀጠለ ነዋሪዎች ተናገሩ።
እስከ አሁን የታሰሩ ሰዎች ቁጥር 245 ደርሷል፤ ሲሉ የተናገሩት ነዋሪዎቹ፣ በእስር ስድስተኛ ሳምንታቸውን ቢያስቆጥሩም፣ ክሥ እንዳልተመሠረተባቸውና የዋስትና መብትም እንደተነፈጉ ገልጸዋል።
ቤተሰቦቻቸውም እንዳይጠይቋቸው እንደተከለከሉና እንደታጎሩበት በገለጹት የፖሊስ ጣቢያው ጠባብ እስር ቤት ውስጥ፣ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እየተፈጸመባቸው እንደኾነ አመልክተዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ እና ምላሽ ለማግኘት፣ ለጋሞ ዞን ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሓላፊ እና ለዞኑ ፖሊስ አዛዥ ስልክ ብንደልላቸውም ስለማያነሡ ለማካተት አልቻልንም።
ይኹንና፣ የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ደግፌ ደበላ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ በሕገ ወጥ አድራጎት የተጠረጠሩ ግለሰቦች እንደታሰሩና ጉዳያቸውም በሕግ አግባብ እንደሚታይ አስታውቀዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም