በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፍልስጤም የመጀመሪያው የሳዑዲ ልዩ መልዕክተኛ ዌስት ባንክን ጎበኙ


የሳዑዲ አምባሳደር ናየፍ አል-ሱዳይሪ
የሳዑዲ አምባሳደር ናየፍ አል-ሱዳይሪ

አዲስ የተሾሙት የፍልስጤም አስተዳደር የሳዑዲ አምባሳደር በእስራኤል ቁጥጥር ስር የምትገኘውን ዌስት ባንክን ለመጀመሪያ ጊዜ ጎበኙ።

ናየፍ አል-ሱዳይሪ በዛሬው ዕለት በዌስት ባንክ ያደረጉት ይህ ጉብኝት፡ በሳዑዲ አረቢያ እና በእስራኤል መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል ለተያዘው ውጥን ‘ብርቱ አጣብቂኝ’ ተደርጎ የሚታየውን ጉዳይ ለመፍታት ዓይነተኛ ሙከራ ተደርጎ ተወስዷል። የሳዑዲ መንግስት ከእስራኤል ጋር ያለው ግንኙነት ወደ መደበኛ ደረጃ ሊሸጋገር የሚችለው ‘በፍልስጤማውያን መንግስት ምሥረታ ጥያቄ ዙሪያ ሁነኛ መሻሻል ሲኖር ብቻ ነው’ ብሏል።

የፍልስጤም ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ባወጣው መግለጫ፡ አል-ሱዳይሪ በፍልስጤም ግዛት ለሁለት ቀናት እንደሚቆዩ አመልክቶ፣ ልዩ መልዕክተኛው “የሁለቱን ሃገሮች ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ያተኩራሉ ብሏል። ከፍልስጤማውያኑ ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ እና ከሌሎች የፍልስጤም ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተው ለመነጋገር ማቀዳቸውም ተዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG