በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፔንታገን ዋና ሀላፊ በአፍሪካ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው


የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን
የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር ሎይድ ኦስቲን ከጂቢቲ መሪዎች እና ከሶማሊያው ፕሬዘዳንት ጋር በጂቡቲ በዛሬው ዕለት ተወያዩ። ይኸ ጉብኝት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአፍሪካ ያደረጉት የመጀመሪያው የስራ ጉብኝታቸው ነው። ሚኒስትሩ በቀጣይ ቀናት ወደ ኬኒያ እና አንጎላ ያቀናሉ።

‘ጅቡቲ ዩናይትድ ስቴትስ በአህጉሪቱ ያላት ከፍተኛ የጦር ሰፈር ነች’ ያሉት ኦስቲን ካምፕ ለሜኑዬ በቀጠናው ጽንፈኞችን ለመዋጋት እና ደህነንትን ለማስጠበቅ ጉልህ የሆነ ሚና አለው ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም ዩናይትድ ስቴትስ በጎረቤት ሀገር ሶማሊያ እየጨመረ የመጣውን የአል ሻባብ አሸባሪ ቡድንን እንቅስቃሴ ለማጥፋት ከአፍሪካ ህብረት ጋር የሚደረገውን ተልዕኮ ለመዋጋት ከጅቡቲ ጋር በመተባበሯ ኩራት ይሰማታል ሲሉ ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለት አንድ ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ እዝ አፍሪኮም በጎርጎሮሳዊያኑ መስከረም 22፣ 2023 ዓ.ም በሶማሊያ የአየር ጥቃት አለማድረጉን አስታውቀዋል።

ይሁን እንጂ አልሻባብ በቴሌግራም ገጹ አፍሪኮም ባደረገው የአየር ጥቃት ስድስት ህጻናትን ጨምሮ ከአንድ ቤተሰብ ውስጥ ስምንት ሰዎችን ገድሏል ሲል ከሷል። በሌላ በኩል የሶማሊያ መንግስት ኢሳቅ አብዱላሂ የተሰኘ የአልሻባብ ቡድን ተልዕኮ ሀላፊ እና የጦር መሪ ከሰባት የግል ጠባቂዎቹ ጋር ባኩል በተሰኘው አካባቢ መግደሉን አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG