በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአለም ችግር እያየለ ሲመጣ የተጋለጠው የመንግስታቱ ድርጅት ጉባዔ


74ኛው የመንግስታቱ ድርጅት ጉባዔ
74ኛው የመንግስታቱ ድርጅት ጉባዔ

የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ የአለም መንግስታትን ለማንቃት ያለመ ጠንከር ያለ ንግግር አድርገዋል። ዋና ጸሀፊው ‘ሊወጡት የማቻል ቀውስ ውስጥ ሆነናል ለታላቅ ክፍፍል ጥቂት ጋት ብቻ ነው የቀረን’ ሲሉ የዓለምን ሁኔታ አስቀምጠዋል።

ግጭት፣ መፈንቅለመንግስት፣ እና ቀውስ በብዙ ቦታዎች እያየሉ መጥተዋል። ዋና ጸሀፊው ባለፉት ዓመታት በባለጸጋዎቹ የሰሜን ሀገራት እና በድሆቹ የደቡብ ሀገራት እንዲሁም በምስራቅ እና በምዕራብ ያለውን ሁኔታ እና በሰው ሰራሽ ልህቀት በኩል ስለታለፈው አዲስ መስመርም በንግግራቸው ማካተታቸው ይታወሳል።

በዚህ ዓመትም “በቀውስ የተሞላ ሽግግር” ነው በማለት የአለም መንግስታት አጣዳፊ የሆነ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል። ጉቴሬስ “አንድ በመሆን ምላሽ መስጠት ያቃተን ይመስላል” በማለት ወቀሳ አቅርበዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG