በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይናው መሪ ደቡብ ኮሪያን ለመጎብኘት እያሰቡ ነው


የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በእስያ ጨዋታዎች መክፈቻ ላይ ሰላምታ ሲሰጡ
የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በእስያ ጨዋታዎች መክፈቻ ላይ ሰላምታ ሲሰጡ

በኮሪያ ባሕረ ሰላጤ (ፔኒንሱላ) ሰላም እና ጸጥታ ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ፣ የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ደቡብ ኮሪያን ለመጎብኘት በቁም ነገር እያሰቡበት እንደሆነ ዮንሃፕ የተሰኘው የደቡብ ኮሪያ የዜና ተቋም ዘግቧል።

የቻይና ማዕከላዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ የሆነው ሲሲቲቪም በበኩሉ ዢ ጂንፒንግ ቅዳሜ እለት ለደቡብ ኮሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃን ዳክ-ሱ፣ ቻይና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ስልታዊ አጋርነት ለማሳደግ ለመስራት ፈቃደኛ መሆኗን እንደገለፁላቸው ዘግቧል።

እ.አ.አ ከ 2014 ወዲህ ደቡብ ኮሪያን እንዳልጎበኙ የተገለፀው ዢ፣ ቅዳሜ እለት ከተጀመረው የእስያ ጨዋታዎች መክፈቻ ቀደም ብሎ፣ በምስራቅ ቻይና በምትገኘው ሃንግጆው ከተማ ከሃን ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸው ታውቋል።

ቻይና ትብብር ለማድረግ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳየቸው፣ ቻይና፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ፣ በመጪው ሳምንት መስከረም 15፣ የሶስትዮሽ ንግግር ለማድረግ ቀነ-ቀጠሮ ከያዙበት ቀን ቀደም ብሎ ሲሆን፣ ሶስቱ ሀገራት ከሶስት አመት በኃላ ለሚያደርጉት ንግግር መንገድ ይጠርጋል ተብሏል።

በተጨማሪም ቻይና፣ በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል የሚደረግ ውይይትን እንደምትደግፍ እና በኮሪያ ባህረሰላጤ ሰላም እና ደህንነት እንዲሰፍን ጥረት እንደምታደርግ ዢ መናገራቸውን ዮንሃፕ ዘግቧ። ሃን በበኩላቸው፣ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ባለው ግንኙነት ዙሪያ፣ ቻይና ገንቢ ሚና እንድትጫወት መጠየቃቸው ተገልጿል።

በዚህ ወር መጀመሪያ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በሩሲያ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል የነበረው ውጥረት የጨመረ ሲሆን፣ ጉብኝቱ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያን አስቆጥቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG