በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል የሚወጣበት ጊዜ እንዲዘገይ ጠየቀች


ፋይል - የዩጋንዳ ሰላም አስከባሪዎች፣ ከአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ልዑክ ጋር በመሆን፣ ሞቃዲሾ ውስጥ ከታጠቀ መኪና አጠገብ ቆመው ይታያሉ።
ፋይል - የዩጋንዳ ሰላም አስከባሪዎች፣ ከአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ልዑክ ጋር በመሆን፣ ሞቃዲሾ ውስጥ ከታጠቀ መኪና አጠገብ ቆመው ይታያሉ።

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ ብሄራዊ የደህንነት አማካሪ የሆኑት ሀሰን ሼክ አሊ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት በፃፉት ደብዳቤ፣ ሁለተኛው ዙር የአፍሪካ ህብረት ልዑክ ወታደሮችን (አትሚስ) የመስወጣት ሂደት ለ90 ቀናት እንዲዘገይ ጠይቀዋል።

የደህንነት አማካሪው በደብዳቤው ላይ ባሰፈሩት መልዕክርት ሶማሊያ "ሦስት ሺ የሚሆኑ የአፍሪካ ህብረት ወታደሮችን የማስወጣቱ ሂደት ለሶስት ወራት እንዲዘገይ በይፋ ትጠይቃለች" ብለዋል።

የተያዘው እቅድ የሚቀጥል ከሆነ የህብረቱ ሦስት ሺህ ወታደሮች በመስከረም መጨረሻ ከሶማሊያ ለቀው እንደሚወጡ በደብዳቤው ተመልክቷል።

እ.አ.አ እስከ 2024 መጨረሻ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሀይሎችን ከሶማሊያ አስወጥቶ ለመጨረስ የተያዘው እቅድ ሶማሊያን አጣብቂኝ ውስጥ የከተታት ሲሆን፣ የተያዘው የጊዜ ገደብ ሳያልቅ፣ በትጥቅ አቅርቦት በደምብ ያልተደራጁት የሶማሊያ የጸጥታ ኃይሎች፣ አልሻባብ በሀገሪቱ መንግስት ላይ የደቀነውን ስጋት መቀልበስ ይችሉ እንደሆን እርግጠኞች አይደሉም።

አስተያየት ለመስጠት ስልጣን እንደሌላቸው በመጥቀስ፣ ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ አንድ ዲፕሎማት ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ የሶማሊያ መንግስት ጊዜው እንዲገፋ የጠየቀው፣ በኢትዮጵያ እና በዩጋንዳ መንግስት የተደገውፈው በሶማሊያ ላይ የተጣለውን የመሳሪያ ማዕቀብ የማንሳት ጥያቄ፣ መልስ እስኪያገኝ ነው።

የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ኃይሎችን በዚህ ሳምንት የማስወጣት ሂደት ከመጀመሩ በፊት፣ ከብሩንዲ፣ ጅቡቲ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ዩጋንዳ የተውጣጡ 20 ሺህ ወታደሮችን በሶማሊያ አሰማርቶ ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG