በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜሌንስኪ ከአሜሪካ ም/ቤት ዓባላት ጋር መከሩ


የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ በምክር ቤቱ የዲሞክራቶች መሪ ሃኪም ጀፈሪስ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ በምክር ቤቱ የዲሞክራቶች መሪ ሃኪም ጀፈሪስ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ፣ ሀገራቸው ከሩሲያ ጋር ለምታካሄደው ጦርነት ከአሜሪካ ድጋፍ ለማግኘት ካፒቶል ይገኛሉ።

በምክር ቤቱ የዲሞክራቶች መሪ ሃኪም ጀፈሪስ አቀባበል የተደረገላቸው ዜሌንስኪ፣ ከሁለቱም ፖርቲ መሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።

አንዳንድ የሪፐብሊካን ዓባላት ለዩክሬን በመፍሰስ ላይ ያለው የአሜሪካ ዶላር ላይ ጥያቄ በማንሳት ላይ ሲሆኑ፣ ፓርቲው ለጦርነት የሚውል ተጨማሪ ዕርዳታን በተመለከተ ያለው ድጋፍ መቀዛቀዙ በመነገር ላይ ነው።

ዜሌንስኪ በተጨማሪም ከፕሬዝደንት ባይደን ጋር በዋይት ሃውስ፣ እንዲሁም ከወታደራዊ መሪዎች ጋር ደግሞ በፔንታጎን እንደሚገናኙ ይጠበቃል።

ከሩሲያ ወረራ ወዲህ ዜለንስኪ አሜሪካንን ሲጎበኙ ለሁለተኛ ግዜ ሲሆን፣ ፕሬዝደንት ባይደን ለምክር ቤቱ የጠየቁት የ 24 ቢሊዮን ዶላር ዕርዳታ እስከ አሁን ውሳኔ አላገኘም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG