በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ለአራተኛ ጊዜ ይወዳደራሉ


የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ
የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ

የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ፣ በቀጣዩ ብሔራዊ ምርጫ ለአራተኛ ጊዜ እንደሚወዳደሩ አስታወቁ፡፡

ትላንት ማክሰኞ በፈረንሳይኛ ቋንቋ ለሚታተመው ዠን አፍሪክ በሰጡት መግለጫ፣ ምዕራባውያን በጉዳዩ ላይ ስለሚኖራቸው አስተያየት የተጠየቁት ካጋሜ፣ “ምዕራቡ ምን እንደሚያስብ የእኔ ችግር አይደለም፤” ሲሉ መልሰዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ፣ የአገዛዛቸውን ዕድሜ ለማቆየት፣ ቀደም ሲል የሥልጣን ጊዜ ገደብን በማራዘማቸው፣ ዩናትይድ ስቴትስ እና ሌሎች ሀገራትም ተችተዋቸው እንደነበር ተወስቷል፡፡

ካጋሜ፣ እ.ኤ.አ በ1994 ከሩዋንዳው ዘር ማጥፋት ጀምሮ የአገሪቱ ብቸኛው መሪ ኾነው ቆይተዋል፡፡

እ.ኤ.አ በ2017 በነበረው ምርጫ 98 ከመቶ ድምፅ በማግኘት አሸናፊ መኾናቸውን ያወጁት የ65 ዓመቱ ካጋሜ፣ እ.ኤ.አ. ከ2000 ጀምሮ ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡

የሥልጣን ዘመናቸውን በማራዘም በአገዛዛቸው ከሰነበቱ የአፍሪካ አገሮች መካከል አንዱ የኾኑት ካጋሜ፣ እ.ኤ.አ. እስከ 2034 ድረስ ሥልጣን ላይ ሊቆዩ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡

በሚቀጥለው ዓመት የሚካሔደው ምርጫ፣ ካጋሜ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ የተወለዱና ሌላ ፕሬዚዳንት የማያውቁ ወጣቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፅ ለመስጠት ብቁ የሚኾኑበት ነው፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG