ከሞሮኮው የመሬት መንቀጥቀጥ የተረፉ ቤተሰቦች፣ ከሳምንት በኋላም፣ በአትላስ ተራሮች ላይ የሞቱትን እየቀበሩ ነው፡፡ ከድንጋይ ናዳዎች ሥር ሰዎችን የማግኘት ተስፋ ግን እየደበዘዘ መጥቷል፡፡
በሬክተር ስኬል 6ነጥብ8 በተመዘገበው ርዕደ መሬት፣ 2ሺሕ900 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፤ 5ሺሕ500 በሚደርሱቱ ላይ አካላዊ ጉዳት ደርሷል፡፡
በተያያዘም፣ ጎርፉ ጠራርጎ የወሰዳቸውን መኖርያ ቤቶች እና የሰዎችን ሕይወት መልሶ መገንባቱም ሌላ ተግዳሮት እንደሚኾን ይጠበቃል፡፡ ሊሳ ብራያንት ከአትላስ ተራሮች የዘገበችውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም