በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ የጥንታዊቷ ኢያሪኮን ፍርስራሽ በዓለም ቅርስነት መዘገበ


በ7ኛው ክፍለ ዘመን የተገነባ ከዌስት ባንክ ከተማ ኢያሪኮ በስተስሜን የሚገኝ፣ እኤአ ጥቅምት. 28, 2021 (ፋይል -ፎቶ)
በ7ኛው ክፍለ ዘመን የተገነባ ከዌስት ባንክ ከተማ ኢያሪኮ በስተስሜን የሚገኝ፣ እኤአ ጥቅምት. 28, 2021 (ፋይል -ፎቶ)

የተባበሩት መንግስታት ጉባዔ የዌስት ባንክ ከተማ በሆነችው ጥንታዊቷ ኢያሪኮ የሚገኙ ፍርስራሾችን በፍልስጤም የዓለም ቅርስ ሆነው እንዲመዘገቡ ድምጽ ሰጠ፡፡

ዛሬ እሁድ የተላለፈው ውሳኔ ግዛቱን የምትቆጣጠረውና ለፍልስጤም ህልውና እውቅና የማትሰጠው እስራኤልን ሳያስቆጣ እንደማይቀር ተገምቷል፡፡

ኢያሪኮ በዓለም እጅግ ጥንታዊ ከሆኑ ህያው ከተሞች መካከል አንዷ ናት፡፡

ከተማዪቱ እስራል በኃይል በተቆጣጠረችው የዌስት ባንክ ውስጥ የምትገኝ ቢሆንም ዓለም አቀፍ እውቅና ባለው የፍልስጤም አስተዳደር ሥር የምትተዳደር መሆኑ በአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ ተጠቅሷል፡፡

በቅርስነት የተመዘገበው የቴል ኤስ ሱልጣን ከክርስቶስ ልደት በፊት በ9ኛው ሺ ዓመተ ዓለም (ሚሊኒየም) የነበሩ ፍርስራሾችን የያዘ ታሪካዊ ስፍራ ነው፡፡

ውሳኔው የተሰጠው በዩኔስኮ አስተባባሪነት፣ ሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ውስጥ በተሰበሰበው የዓለም ቅርስ ኮሚቴ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል፡፡

ዘመናዊቷ የኢያሪኮ ከተማ በታሪካዊ ቦታዎቿ እና ለሙት ባህር (the Dead Sea ) ባላት ቅርበት ምክንያት ለፍልስጤም ግዛቶች ትልቅ የቱሪዝም መስህብ መሆኗ ተመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG