No media source currently available
ሙሉ ለሙሉ በአፍሪካዊያን የተሰራ ተከታታይ የአኒሜሽን ፊልም በኔትፍሊክስ የፊልም አውታር ላይ ለዕይታ ቀርቧል። የዛምቢያዋ መዲና ሉሳካን በመጪው ዘመን የሳለው ‘ሱፓ ቲም ፎር’ የተሰኘው የአኒሜሽን ፊልም በወጣት ዛምቢያዊት የፊልም ጸሀፊ የተዘጋጀ ነው። የፊልሙ በአለም አቀፍ ገበያ ላይ መታየት ለአፍሪካዊያን የአኒሜሽን እና የፈጠራ ባለሞያዎች በር ከፋች እንደሆነ ባለሞያዎች እየተናገሩ ነው።