በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሺሕ የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች በአንድ ቀን ውስጥ መግባታቸው ጣሊያንን አስጨንቋል


ስደተኞች በላምፔዱሳ የስደተኞች መቀበያ ማዕከል፣ ሲሲሊ እእአ 14/2023
ስደተኞች በላምፔዱሳ የስደተኞች መቀበያ ማዕከል፣ ሲሲሊ እእአ 14/2023

በጣሊያን ላምፔዱሳ ደሴት የሚገኝ የስደተኞች መቀበያ፣ በብዛት ሆነው አዲስ በደረሱ ፍልሰተኞች ምክንያት ከገድብ በላይ በመሙላቱ፣ ባለሥልጣናት በሺሕ የሚቆጠሩ ስደተኞችን ወደ ዋናው የጣሊያን ምድር ለማስተላለፍ በመጣር ላይ ናቸው።

አዛውንቶች የሚበዙበት የጣሊያን ሕዝብ እና የኢኮኖሚ ችግር ሕገ ወጥ ፍልሰተኞችን በማስገባት አይፈታም”

በሺሕ የሚቆጠሩ እና ከቱኒዚያ የተነሱት ፍልሰተኞች በ120 ጀልባዎች በመሆን በ24 ሰዓታት ውስጥ በመግባታቸው ከፍተኛ መጨናነቅ ተከስቷል ሲል ቀይ መስቀል አስታውቋል። መቀበያ ጣቢያው በመሙላቱ ከፊሎቹ ፍልሰተኞች በደሴኢቱ የተለያዩ ክፍሎች ታይተዋል። ነዋሪዎች ለፍልሰተኞቹ ምግብ እና ውሃ ሲያድሉ ተስተውለዋል።

በአጠቃላይ 6 ሺሕ 800 የሚሆኑ ፍልሰተኞች ደሴቲቱ መድረሳቸው ተመልክቷል።

“ጣሊያን ችግሩን ብቻዋን እንድትጋፈጥ አድርጓል” ሲሉ የላምፔዱሳ ከንቲባ ፊሊፖ ማኒኖ የአውሮፓ ኅብረት ላይ ወቀሳ አቅርበዋል።

“አዛውንቶች የሚበዙበት የጣሊያን ሕዝብ እና የኢኮኖሚ ችግር ሕገ ወጥ ፍልሰተኞችን በማስገባት አይፈታም” ሲሉ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጂዮርጂያ ሜሎኒ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG