በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሥልጡኑ የዋሻ ውስጥ ተጓዥ አሜሪካዊ ከአደጋ ቢተርፍም ጉዞውን እንደሚቀጥል አስታወቀ


አሜሪካዊው የዋሻ ጉዞ አዘውታሪው ማርክ ዲኪ በደቡብባዊው ቱርክ እአአ መስከረም 12/2023
አሜሪካዊው የዋሻ ጉዞ አዘውታሪው ማርክ ዲኪ በደቡብባዊው ቱርክ እአአ መስከረም 12/2023

የቱርክ እና ዓለም አቀፍ የዋሻ ውስጥ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች፣ ባለፈው ማክሰኞ፣ ሕይወቱን ከዋሻ ውስጥ የታደጉት አሜሪካዊ ሥልጡን የዋሻ ተጓዥ፣ ወደፊትም በዋሻ ውስጥ ጊዜ ማሳለፉን እንደሚቀጥል አስታወቀ።

አሜሪካዊው የዋሻ ጉዞ አዘውታሪው፣ ከአንድ ሺሕ ሜትር በላይ ጥልቀት ካለው ዋሻ ውስጥ፣ በሕመም ምክንያት መውጣት ሳይችል ቀርቶ በአደጋ ላይ ነበር፡፡

የ40 ዓመት ዕድሜ ያለው ማርክ ዲኪ፣ በደቡብ ቱርክ የሚገኘውንና 1ሺሕ276 ጥልቀት ያለውን ዋሻ ካርታ ለመሥራት በሚሞክርበት ወቅት፣ አንድ ሺሕ ሜትር ርቀት ላይ እንዳለ በመታመሙና መንቀሳቀስ ባለመቻሉ፣ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችን ትድግና ለ11 ቀናት ለመጠባበቅ ተገዶ ነበር።

ከዋሻው ከወጣበት ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ፣ በሆስፒታል ሕክምና በማግኘት ላይ እንደኾነ የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።

ከሆስፒታል ኾኖ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጠው ማርክ ዲኪ፣ በዋሻው ሰዎች እንዲደርሱለት በመጠበቅ ላይ ሳለ ተስፋ እንዳልቆረጠ ተናግሯል። አሁንም ወደ ዋሻው መመለስ እንደሚፈልግና ዋሻዎችን መቃኘት ሳይንሳዊ ጠቀሜታ እንዳለው ጨምሮ ገልጿል።

ማርክ ዲኪን ከዋሻው ለማውጣት፥ ከቱርክ፣ ከጣልያን፣ ከክሮሺያ እና ከሌሎችም ሀገራት የተውጣጡ 150 የአደጋ ሠራተኞች እንደተሳተፉ ታውቋል። የሠለጠነ የዋሻ ውስጥ ተጓዥ እና እርሱም የዋሻ ውስጥ አደጋ ታዳጊ እንደኾነ የተነገረለት ማርክ ዲኪ፣ በዓለም አቀፍ የዋሻ አደጋዎች ወቅት በቀድሞ ደራሽነቱ እንደሚታወቅ ተነግሯል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG