- ኀይል በተቀላቀለበት ምርመራ በተገደለው አርሶ አደር አራት የፀጥታ ኅይሎች ተያዙ
በትግራይ ክልል የደቡባዊ ዞን ከፍተኛ አመራር፣ ትላንት ማክሰኞ ምሽት፣ በማይጨው ከተማ፣ ከአንድ ግለሰብ በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ፡፡
በግድያው የተጠረጠረው ግለሰብ፣ ገና በቁጥጥር ሥር እንዳልዋለ፣ የዞኑ ፖሊስ የሰው ኀይል አስተዳደር ሓላፊ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡
በሌላ የግድያ ዜና፣ ባለፈው ሳምንት፣ በክልሉ ሰሜን ምዕራብ ዞን ፅምብላ ወረዳ፣ አንድ አርሶ አደር፣ በጸጥታ አካላት ታስሮ በተፈጸመበት ድብደባ ሕይወቱ እንዳለፈ፣ ወንድሙ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል፡፡
የወረዳው የጸጥታ እና አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ሓላፊ፣ አርሶ አደሩ፣ ኀይል ከተቀላቀለበት ምርመራ የተነሣ ሕይወቱ እንዳለፈ አምነው፣ ጉዳዩ እየተጣራ እንደኾነ አስታውቀዋል።
የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የማያውቃቸው እስር ቤቶች መኖራቸውን፣ ባለፈው ሳምንት፣ አቶ ጌታቸው ረዳ በሰጡት መግለጫቸው ላይ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም