በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዐዲሱ ዓመት ግጭቶችን በሕግ እና ፖለቲካዊ ማኅቀፎች በዘላቂነት ለመፍታት ትኩረት እንዲሰጥ ኢሰመኮ ጠየቀ

በዐዲሱ ዓመት ግጭቶችን በሕግ እና ፖለቲካዊ ማኅቀፎች በዘላቂነት ለመፍታት ትኩረት እንዲሰጥ ኢሰመኮ ጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:20 0:00

በዐዲሱ ዓመት ግጭቶችን በሕግ እና ፖለቲካዊ ማኅቀፎች በዘላቂነት ለመፍታት ትኩረት እንዲሰጥ ኢሰመኮ ጠየቀ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በ2015 ዓ.ም. በአገሪቱ የተስፋፉ የትጥቅ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አበረታች ጥረቶች ቢደረጉም፣ አሁንም አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እየተፈጸሙ እንደኾ ጠቅሷል። ጥሰቶቹ በዐዲሱ ዓመት እንዳይቀጥሉ፣ በሕግ ማኅቀፍ ዘላቂ መፍትሔ መስጠት እንደሚገባም አሳስቧል።

የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መለሰ እንደተናገሩት፣ በግጭቶች እና ጥቃቶች ሳቢያ በዜጎች በሕይወት የመኖር እና የመንቀሳቀስ መብት ላይ እየደረሰ ያለው ጥሰት አሳሳቢ ነው፡፡

በየአካባቢው የተስፋፉ ግጭቶች የሰብአዊ መብቶችን ጥሰት እንዳስከተሉ ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩት በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር በፈቃዱ ድሪባም፣ ከወታደራዊ ርምጃ ይልቅ ፖለቲካዊ መፍትሔ፣ ለግጭቶቹ ዘላቂ እልባት ለመስጠት እንደሚያስችል አመልክተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG