በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግጭት የታወከው የዐማራ ክልል ትራንስፖርት እና ከጉዞ የተስተጓጎሉት ነዋሪዎች ተስፋ


በግጭት የታወከው የዐማራ ክልል ትራንስፖርት እና ከጉዞ የተስተጓጎሉት ነዋሪዎች ተስፋ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:13 0:00

በግጭት የታወከው የዐማራ ክልል ትራንስፖርት እና ከጉዞ የተስተጓጎሉት ነዋሪዎች ተስፋ

በዐማራ ክልል በተስፋፋው የትጥቅ ግጭት ምክንያት፣ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ባለመኖሩና ጸጥታውም አስተማማኝ ባለመኾኑ፣ በዓልን ከቤተሰቦቻቸው ጋራ ማክበር እንዳልቻሉ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሠሪዎች ፌዴሬሽን፣ ከዐዲስ አበባ ወደ ጎጃም የሚደረገው የሕዝብ ትራንስፖርት ስምሪት ከተቋረጠ ሳምንታት እንዳለፈው አረጋግጧል፡፡ በደሴ በኩል ወደ ክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የሚደረገው ጉዞ ግን እንደቀጠለ አመልክቷል፡፡

ነገ የሚብተውን ዐዲሱን ዓመት አስመልክቶ ያናገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች፣ በ2015 ዓ.ም. የታየው የጸጥታ መደፍረስ የማይደገምበት፣ ሰላም የሚሰፍንበትና የሰዎች የእንቅስቃሴ ነፃነት ያለገደብ የሚከበርበት ዓመት ይኾን ዘንድ ተመኝተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG