በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ኅብረት ቡድን 20ን በመቀላቀሉ የኅብረቱ ፕሬዚደንት ደስታቸውን ገለጹ


የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንዲራ ሞዲ፣ የአፍሪካ ኅብረት ፕሬዚደንት አዛሊ አሱማኒ
የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንዲራ ሞዲ፣ የአፍሪካ ኅብረት ፕሬዚደንት አዛሊ አሱማኒ

የአፍሪካ ኅብረት ፕሬዚደንት አዛሊ አሱማኒ፣ ኅብረቱ የቡድን 20 ዓባል በመሆኑ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ትናንት እሁድ በሰጡት መግለጫ "በጣም ደስ ብሎኛል፣ በመሪዎቹ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ዓባልነቱ ጸድቋል” ብለዋል፡፡ “የተከበሩ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ እና የቡድን 20 ዓባላት የአፍሪካ ኅብረት ወደዚህ ትልቅ የኢኮኖሚ ውሳኔ ሰጪ አካል መቀላቀልን ደግፈዋል" ሲሉም አክለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ስለ ቡድኑ ዓባልነት ጠቀሜታ ሲገልጹም፣ "በትክክል ብዙ ይረዳል። አፍሪካ በእርግጥ ውስጣዊ ጉዳዮች አሏት። ለእነዚያ ጉዳዮች መፍትሄ ማፈላለግ አለባት” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“ይሁን እንጂ በጋራ በሚሠራበት በዚህ ዘመን፣ ብቻችንን መሥራት አንችልም፣ በአህጉሪቱ የሚገኙ ሀገራት በጋራ መሥራት አለባቸው፣ አፍሪካ ላሉባት ጉዳዮች መፍትሔ ለመሻት የቡድን 20 ሀገራት ያግዙናል”

“ይሁን እንጂ በጋራ በሚሠራበት በዚህ ዘመን፣ ብቻችንን መሥራት አንችልም፣ በአህጉሪቱ የሚገኙ ሀገራት በጋራ መሥራት አለባቸው፣ አፍሪካ ላሉባት ጉዳዮች መፍትሔ ለመሻት የቡድን 20 ሀገራት ያግዙናል” በማለት ከሌሎች ጋር የመስራት አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

55 አባላት ያሉት የአፍሪካ ኅብረት፣ ለተሻለ የቡድን ውክልና ከአውሮፓ ኅብረት እኩል በይፋ የቡድን 20 ቋሚ አባል መደረጉ ተመልክቷል፡፡ እስከ አሁን የቡድን 20 ዓባል የነበረችው ደቡብ አፍሪካ ብቻ ነበረች፡፡

የአፍሪካ ኅብረት መወከል የቡድን 7 ሀገራት የበላይነቱን ሲጫወቱ በቆዩበት በ ቡድን 20 ውስጥ፣ ለደቡቡ የዓለም ክፍል ትልቅ ድምፅ ይሆነዋል ተብሏል።

የአባልነቱ ውሳኔ የመጣው በቻይና እና ሩሲያ የበላይነት ቁጥጥር ያለው ብሪክስ የተሰኘው ቡድን፣ ሳዑዲ ዓረብያን፣ ኢራንን እና ሌሎችንም ጨምሮ በመስፋፋት፣ ብሪክስን የቡድን 20 አማራጭ ለማድረግ ቤጂንግ ጥረት በማድረግ ላይ ነች በሚባልበት ወቅት ነው። በሌላ በኩል፣ የኅብረቱ ፕሬዝደንት ሞሮኮ ውስጥ በሪክተር መለኪያ 6.8 እንደሚሆን በተገመተው ርዕደ መሬት 2100 የሚሆኑ ሰዎች በመሞታቸው የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG