በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የቆየውን የቻይና ጉዞ ይፋ አደረጉ


የአውስትራሊያ የቀድሞ የንግድ ሚኒስትር ክሬግ ኤመርሰን እና የቻይና የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊ ዣኦክሲንግ በቻይና እና አውስትራሊያ አመራሮች ውይይት ላይ ተገናኝተው ሲጨባበጡ - መስከረም 7፣ 2023
የአውስትራሊያ የቀድሞ የንግድ ሚኒስትር ክሬግ ኤመርሰን እና የቻይና የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊ ዣኦክሲንግ በቻይና እና አውስትራሊያ አመራሮች ውይይት ላይ ተገናኝተው ሲጨባበጡ - መስከረም 7፣ 2023

አውስትራሊያ ከቻይና ጋር የገባችውን የንግድ እሰጥ አገባ ለመፍታት በምታደርገው ጥረት የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር አንተኒ አልባኔዝ በዚህ አመት ወደ ቻይና እንደሚጓዙ አስታውቀዋል።

እ.አ.አ ከ2016 ዓ.ም ወዲህ የአውስትራሊያ መሪ ወደ ቻይና ሲጓዝ የመጀመሪያው ይሆናል።

ግራ ዘመም የሆነው የአልባናዚ መንግስት ባለፈው አመት ግንቦት ላይ በተካሄደው ምርጫ ስልጣን ከተረከበ ወዲህ፣ ዋና የንግድ አጋሩ ከሆነው ቻይና ጋር የገባበትን ፍጥቻ ለማቆም ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ቻይና የድንጋይ ከሰል፣ ገብስ እና ወይንን ጨምሮ በተለያዩ የአውስትራሊያ ምርቶች ላይ የንግድ ማዕቀብ ጥላለች። በሁለቱ ሀገራት መካከል ለተፈጠረው ዲፕሎማቲክ ውጥረት ምክንያት የሆነው የሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ በደቡብ ቻይና ባህር ያለው እንቅስቃሴ ነፃነት እና የታይዋን ጉዳይ መሆኑን ተንታኞች ይገልፃሉ።

ቀድሞ የነበረው የአውስትራሊያ ወግ አጥባቂ መንግስት፣ የኮቪድ 19 አመጣጥ ላይ ጠንካራ ምርመራ እንዲደረግ በመደገፉም ቻይናን አስቆጥቶ ነበር።

አዲሱ መንግስት ስልጣን ከተረከበ በኃላ ግን ሁለትዮሽ ግንኙነቱ በተወሰነ መልኩ እየተሻሻለ ሲሆን፣ ቻይና በአውስትራሊያ ምርቶች ላይ ጥላው የነበረውን የተወሰኑ ገደቦችም አንስታለች።

አልባኒዝ በዚህ አመት ወደ ቤይጂንግ እንደሚጓዙ ይግለፁ እንጂ ቀኑ በትክክል መቼ እንደሚሆን ይፋ አልተደረገም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG