በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሽኖዬ ባህላዊ የልጃገረዶች ጨዋታን የማስቀጠል ዐውደ ትርኢት በአምቦ


ሽኖዬ ባህላዊ የልጃገረዶች ጨዋታን የማስቀጠል ዐውደ ትርኢት በአምቦ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:36 0:00

ሽኖዬ ባህላዊ የልጃገረዶች ጨዋታን የማስቀጠል ዐውደ ትርኢት በአምቦ

በኦሮሞው የገዳ ሥርዐት፣ ጭጋጋማው የሦስት ወር ክረምት እየገፈፈ፣ የብሩህ ተስፋ ምልክት ወደኾነው የመፀው ወራት ሲታለፍ፣ ምስጋና የሚቀርብባቸውና ልዩ ልዩ መልዕክት የሚተላለፍባቸው ባህላዊ የጨዋታ ክዋኔዎች አሉ፡፡ ከእነርሱም አንዱ የሽኖዬ ባህላዊ ጨዋታ ነው።

ሽኖዬ፣ በልጃገረዶች የሚከወን ባህላዊ ጨዋታ ነው፡፡ ሰሞኑን፣ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ከተማ፣ ጨዋታውን እየከወኑ ያሉት ልጃገረዶች፣ የከተማው ልዩ ትዕይንት ኾነው ይታያሉ።

በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን የባህል ጥናት እና ምርምር ማዕከል የሚያስተባብረው ይኸው የክዋኔ መርሐ ግብር፣ የሽኖዬን ባህላዊ ጨዋታ ለኅብረተሰቡ ከማዘከር ባለፈ፣ ነባር ይዘቱን እንደጠበቀ ለትውልድ እንዲተላለፍ የማስጠበቅ ዓላማ እንዳለው ማዕከል አመልክቷል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG