በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሌ ክልል የጎሣ መሪዎች የአማካሪ ምክር ቤት ተቋቋመ


የሶማሌ ክልል የጎሣ መሪዎች የአማካሪ ምክር ቤት ተቋቋመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:14 0:00

የሶማሌ ክልል የጎሣ መሪዎች የአማካሪ ምክር ቤት ተቋቋመ

የሶማሌ ክልል፣ የክልሉን የጎሣ መሪዎች ያካተተ የአማካሪ ምክር ቤት አቋቁሟል።

አማካሪ ምክር ቤቱ፣ በክልሉ የሚከሠቱ ግጭቶችን በመፍታት ረገድ ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል፡፡ በልማት ዕቅዶች እና ትግበራዎች ላይም የማይናቅ ሚና እንደሚኖራቸው ተመልክቷል።

የምክር ቤቱን መቋቋም በበጎ እንደሚያዩት የገለጹ፣ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ባለሞያ፣ አማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች መጠቀምን ከሚያበረታታው ሀገራዊ የሕግ ማሻሻያ ጋራ የሚጣጣም ነው፤ ብለዋል።

ኾኖም፣ የጎሣ መሪዎቹ ምክር ቤት፣ ፖለቲካዊ ሥልጣንም ይኑረው፤ ከተባለ፣ በአንድ ወገን ተጽእኖ ሥር ሊወድቅ ስለሚችል፣ ሚናው በአማካሪነት መገደቡ ተገቢ እንደኾነ፣ የሕግ ባለሞያው አስረድተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG