በዘላቂው ሉላዊ የልማት ግቦች፣ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት፣ የሁሉ አቀፍ የጤና ሽፋን መሠረት ቢሆንም፣ በጤናው ዘርፍ በተሰማሩ ባለሞያዎች ዘንድ ሳይቀር የተሳሳተ ግንዛቤ እንደተሰጠው፣ በዐዲስ አበባ እየተካሔደ በሚገኝ አንድ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ተጠቆመ፡፡
ዓለም አቀፍ ጉባኤው፣ በቀጣይ የሥራ ጊዜው፥ ጠንካራ ፖለቲካዊ ምርጫዎችን ስለ ማድረግ፣ ዘላቂ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት ስለ መገንባት እና በመሳሰሉት መሪ ሐሳቦች ላይ ተመሥርቶ እንደሚወያይ ታውቋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም