በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳኑ አል ቡርሃን ወደ ኳታር አቀኑ


ፎቶ ፋይል፦ የሱዳኑ ጦር ጠቅላይ አዛዥ ጀኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን፣ ካርቱም፤ ሱዳን እአአ ታኅሳስ 5/2022
ፎቶ ፋይል፦ የሱዳኑ ጦር ጠቅላይ አዛዥ ጀኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን፣ ካርቱም፤ ሱዳን እአአ ታኅሳስ 5/2022

የሱዳኑ ጦር ጠቅላይ አዛዥ ጀኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ከኳታሩ መሪ ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ ጋር ለመነጋገር ወደዛች ሀገር ማቅናታቸውን የሱዳን መንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

የኳታሩ ጎዞ የመጣው ሌሎች ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች በግብጽ እና በደቡብ ሱዳን መደረጋቸውን ተከትሎ ነው።

የሱዳን ጦር በለቀቀው ቪዲዮ አል ቡርሃን በዶሃ፣ ኳታር ሲደርሱ እና የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ሲቀበሏቸው ታይቷል። በመንግስት የሚተዳደረውየኳታር ዜና አገልግሎትም አል ቡርሃን ዶሃ እንደሚገኙ አረጋግጧል።

በሱዳን ሁሉን አቀፍና ሁሉንም የፖለቲካ ኃይሎች የሚያሳትፍ የሰላም ውይይት እንዲደረግ፣ የኳታሩ አል ታኒ በውይይቱ ወቅት ጥሪያቸውን ደግመው አስተላልፈዋል። አል ቡርሃን ከከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው ጋር መጓዛቸውም ታውቋል።

አል ቡርሃን ባልፈው ሰኞ ከደቡብ ሱዳኑ መሪ ሳልቫ ኪር ጋር ጁባ ውስጥ የተገናኙ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት ደግሞ ወደ ግብጽ አቅንተው ከፕሬዝደንት አል ሲሲ ጋር ተወያይተዋል። ሁለቱንም ጉብኝቶች በተመለከተ ዝርዝር ጉዳዮች አlወጡም።

በሱዳን በመካሄድ ላይ ያለው ግጭት ቢያንስ የ 4ሺሕ ሰዎች ሕይወትን ሲቀጥፍ፣ ከ 5 ሚሊዮን በላይ ደግሞ መፈናቀላቸውን ተመድ አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG