በዐዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥር በተዋቀረችው የስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ በቅበት ከተማ ነዋሪዎች እና በጸጥታ ኃይሎች መካከል፣ ትላንት በተፈጠረና የሃይማኖት መልክ እንዳለው በተገለጸ ግጭት፣ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ፣ የቆሰሉ እና የተፈናቀሉ ሰዎችም መኖራቸውን፣ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የግጭቱ መነሾ፣ “በከተማዋ ከተደረገብን መተት የተነሣ ለሕመም ተዳርገናል፤” ያሉ የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ “የመተቱን መንፈስ ከከተማዪቱ ለማባረር” በሚል፣ በድምፅ ማጉያ ቁርዐን ለመቅራት ወደ ጎዳና የወጡ ወጣቶች፣ ከጸጥታ ኃይሎች ጋራ በመጋጨታቸው ነው፤ ሲሉ ነዋሪዎቹ አስረድተዋል።
በግጭቱ ጥቃትን የሸሹ ከአንድ ሺሕ በላይ የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ ከከተማው ተፈናቅለው በቡታጅራ የቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው እንደሚገኙ፣ ተፈናቃይ የቅበት ነዋሪዎች፣ በስልክ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
ማንነታቸውን ያልጠቀሱ የቅበት ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ባልደረባም፣ የሃይማኖት መልክ ያለው ግጭት በከተማው ተፈጥሮ እንደነበረና አኹን ግን ወደ መረጋጋት መመለሱን ገልጸዋል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ)
መድረክ / ፎረም