በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር መሪ ላይ ማዕቀብ ጣለች


ፋይል - በሱዳን የፈጥኖ ደራሽ አዛዥ አብደልራሂም ሃምዳን ደጋሎ
ፋይል - በሱዳን የፈጥኖ ደራሽ አዛዥ አብደልራሂም ሃምዳን ደጋሎ

ዩናይትድ ስቴትስ በሱዳን የፈጥኖ ደራሽ አዛዥ አብደልራሂም ሃምዳን ዳጋሎ ላይ፣ ወታደሮቻቸው ከሱዳን ጦር ጋር ለወራት በዘለቀው ግጭት ባደረሱት ጥቃትና የሰብአዊ መብት ረገጣ ማዕቀብ የጣለችባቸው መሆኑን አስታወቀች፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ዳጋሎን የከሰሰችው "ለሲቪሎች ጭፍጨፋ፣ የዘር ግድያ እና የፆታዊ ጥቃት " ተጠያቂ የሆኑትን የወታደሮች ቡድን በመምራታቸው” መሆኑን የአሶሴትይድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

ዛሬ ረቡዕ የወጣው የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር መግለጫ ማዕቀቡ የፈጥኖ ደራሹ ጦር መሪ፣ የመሀመድ ሃምዳን ዳግሎ ወንድም መሆናቸውን በገለጸው “በአብደልራሂም ሃምዳን ዳጋሎ የተያዙና ዩናይትድ ውስጥ የሚገኙ ንብረቶች እና ተየያዥ ይዞታዎችን በሙሉ” ያገደ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ዛሬ ረቡዕ የተጣለው ማዕቀብ ግጭቱ ከተጀመረ ወዲህ ግለሰብን ኢላማ በማድረግ በዩናይትድ ስቴትስ የተጣለና ይፋ የተደረገ የመጀመሪያው ማዕቀብ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

ባላፈው ሰኔ ዩናይትድ ስቴት ከሱዳን ጦርም ሆነ ከፈጥኖ ደራሹ ጦር ጋር ግንኙነት ወይም ባለቤትነት ባላቸው አራት ቁልፍ ተቋማት ላይ ማዕቀቦችን መጣሏ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG