በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ — ለወራት በዘለቀው የሱዳኑ ግጭት ከ5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል


ፋይል - በጦርነት ከሚታመሰው ሱዳን የሸሹ ሴቶች፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሬንክ ከተማ ከሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት የመሸጋገሪያ ማዕከል፣ ምግብ ለመቀበል ተሰልፈው ይታያሉ
ፋይል - በጦርነት ከሚታመሰው ሱዳን የሸሹ ሴቶች፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሬንክ ከተማ ከሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት የመሸጋገሪያ ማዕከል፣ ምግብ ለመቀበል ተሰልፈው ይታያሉ

በሱዳን ለወራት በዘለቀው ውጊያ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት የፍልስተኞች ጉዳይ ድርጅት አስታወቀ፡፡

በአገሪቱ ጦር ሠራዊትና እና በተቀናቃኙ የፈጥኖ ደራሽ ጦር መካከል ባላፈው ሚያዝያ አጋማሽ የተቀሰቀሰው ግጭት ምንም ዓይነት የመረጋጋት ምልክት አላማሳየቱን አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት (አይ ኦ ኤም) ዛሬ ረቡዕ እንዳስታወቀው በግጭቱ ከ4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በአገር ውስጥ ተፈናቅለዋል፡፡ ከ 1.1 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ ወደ አጎራባች አገሮች ተሰደዋል፡፡

ከ750ሺ በላይ የሚሆኑት ወደ ግብጽ ወይም ቻድ የተሰደዱ መሆናቸውንም አይኦኤም ገልጿል፡፡

እስካሁን ግጭቱን ለመሸምገል የተደረጉ ዓለም አቀፍ ጥረቶች መክሸፋቸው ተመልክቷል፡፡

ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት ጀምሮ ቢያንስ ስምንት የተኩስ አቁም ስምምነቶች የተካሄዱ ሲሆን ሁሉም ተጥሰው ጦርነቱ መቀጠሉ ተገልጿል፡፡

ካርቱምን ወደ ትንሽ የከተማ ውስጥ ጦር ሜዳ ዝቅ ማድረጉ በተነገረለት ውጊያ ከተፋላሚዎቹ አንዳቸውም ከተማዪቱን መቆጣጠር አለመቻላቸውን የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG