በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከን ለድንገተኛ ጉብኝት ኪቭ ናቸው


የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይፋ ባደረገው በዚህ ፎቶ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በስተቀኝ እና የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሚትሮ ኩሌባ፣ የጀግኖች መቀበሪያ ስፍራ በሆነው እና ኪቭ በሚገኘው በርኮቭስኬ የቀብር ስፍራ ሲያልፉ ይታያሉ - መስከረም 6፣ 2023
የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይፋ ባደረገው በዚህ ፎቶ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በስተቀኝ እና የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሚትሮ ኩሌባ፣ የጀግኖች መቀበሪያ ስፍራ በሆነው እና ኪቭ በሚገኘው በርኮቭስኬ የቀብር ስፍራ ሲያልፉ ይታያሉ - መስከረም 6፣ 2023

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ሩሲያ በሳምንቱ ውስጥ የመጀመሪውን የሚሳዬል ጥቃት ከጀመረች ከሰዓታት በኋላ፣ በድንገት ዛሬ ረቡዕ ለጉብኝት ዩክሬን ዋና ከተማ ኪቭ ገብተዋል፡፡

ብሊንክን የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲምትሮ ኩሌባን ያነጋገሩ ሲሆን ከፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለነስኪ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዴኒስ ሽማያል ጋር ተገናኝተው ስለ መልሶ ማጥቃቱና መልሶ መገንባት ጥረቶች ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

"ዩክሬን ውስጥ መሆን እና ወደ ዩክሬን መመለስ ሁልጊዜ ጥሩ እና አበረታች ነው” ያሉት ብሊከን “ እ.አ.አ. በየካቲት 2022 ከጀመረው የሩሲያ ወረራ ወዲህ፣ ዩክሬን ውስጥ ስሆን ይህ አራተኛ ጊዜዬ ነው፡፡ ሁልጊዜም እዚህ በሆንኩ ጊዜ ፣ የዩክሬን ሰዎች፣ የዩክሬን ኃይሎች እና የዩክሬን አመራር ያልተለመደ ጽናትና ጀግንነት ያስደንቀኛል” ብለዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት የብሊንከን ጉብኘት የዩክሬንን የሶስት ወራት መልሶ ማጥቃት ለመገመገም ነው፡፡

አንዳንድ ምዕራባውያን አጋሮች የሰላም ስምምነቱን አስመልክቶ ስጋታቸውን በሚገልጹበት ወቅት የተካሄደው ይህ ጉብኝት ከ19 ወራት ጦርነት በኋላ ኪቭ የክሬምሊን ኃይሎች ለማስወጣት የምታደርገውን ጥረት፣ ዩናይትድ ስቴትስ መደገፏን የምትቀጥል መሆኑን ፍንጭ ለመስጠት እንደሆነ ባለሥልጣናቱ አመልክተዋል፡፡

ብሊንከን ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የምትሰጠውን ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ አዲስ የገንዘብ ድጋፍ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG