በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፋኖ የታገቱ ሰዎች ደህንነት እንዳሳሰባቸው ቤተሰቦቻቸው አስታወቁ


በፋኖ የታገቱ ሰዎች ደህንነት እንዳሳሰባቸው ቤተሰቦቻቸው አስታወቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:14 0:00

በፋኖ የታገቱ ሰዎች ደህንነት እንዳሳሰባቸው ቤተሰቦቻቸው አስታወቁ

በቅርቡ በፋኖ ታጣቂ ቡድን አባላት የታገቱት ሰዎች የደህንነት ጉዳይ እንዳሳሰባቸው በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣የመንዲዳ ከተማ ነዋሪ የኾኑ ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ በአገሪቱ እየተካሄዱ ባሉ የትጥቅ ግጭቶች ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ አካላት ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ከማድረግ እንዲቆጠቡ አሳሰቧል።

በቅርቡ በፋኖ ታጣቂ ቡድን አባላት መታገታቸው ስለተገለጸው በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣የመንዲዳ ነዋሪ የሆኑ ስምንት ሰዎች ጉዳይ የተጠየቁት የኮሚሽኑ ክልላዊ ዳይሬክተር ኢማድ አብዱልፈታ "በዕገታ ስር ያሉ ካሉ" እንዲለቀቁ ጥሪ እናቀርባለን ብለዋል።

ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ማድረግ በኢትዮጵያም ኾነ በዓለምአቀፍ ሕጎች የሚያስጠይቅ ወንጀል እንደኾነም ተናግረዋል ።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ያገኛሉ)

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG