በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ኮሪያው መሪ ሩሲያን ሊጎበኙ ይችላሉ


ፋይል - እ.አ.አ በሐምሌ 27፣ 2023 የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን በፒዮንግያን ለሩሲያ ጦር ልዑክ ባዘጋጁት ግብዥ ላይ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌ ሻይጉ ተገኝተው ነበር (ሮይተርስ ፎቶ)
ፋይል - እ.አ.አ በሐምሌ 27፣ 2023 የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን በፒዮንግያን ለሩሲያ ጦር ልዑክ ባዘጋጁት ግብዥ ላይ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌ ሻይጉ ተገኝተው ነበር (ሮይተርስ ፎቶ)

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለመገናኘት ወደዛች ሀገር ሊያቀኑ እንደሚችሉ የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

ኪም ጆንግ ኡን የተባለውን ጉዞ የሚያደርጉ ከሆነ፣ በየፊናቸው ከአሜሪካ ጋር መፋጠጥ ውስጥ በገቡት በሁለቱ ሃገራት መካከል ጠንካራ ትብብር እንዳለ አመላካች ይሆናል።

ኪም ጆንግ ኡን፤ በዩክሬን ጦርነት የጦር መሣሪያዋ እየተሟጠጠባት ላለው ሩሲያ መሣሪያ ለማቅረብ ቃል ሊገቡ ይችላሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ በምትኩም የምግብ፣ የኃይል እና የዘመናዊ መሣሪያ ቴክኖሎጂዎችን ከሩሲያ እንደሚጠብቁ ሪፖርቱ ጠቁሟል።

ሞስኮ እና ፒዮንግያንግ የመጀመሪያውን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሊያደርጉ እንደሚችሉም የሩሲያው መከላከያ ሚኒስትር አስታውቋል።

ሩሲያ የዩክሬንን መልሶ ማጥቃት ለማምከን ስትሻ፣ ሰሜን ኮሪያ በበኩሏ አሜሪካ ከደቡብ ኮሪያ እና ከጃፓን ጋር ያላትን ወታደራዊ ቃል ኪዳን በመቃወም በርካታ የሚሳኤል ሙከራዎችን አድርጋለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG