በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓረብ ኤምሬትስ ለአፍሪካ ለንጹህ ኃይል ግንባታ 4.5 ቢሊዮን ዶላር ቃል ገባች


የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ መጀመሩን ተከትሎ፣ በአየር ንበረት ለውጥ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የሚጠይቁ ተቃዋሚዎች በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ጎዳናዎች ላይ ጥያቄ ሲያቀርቡ
የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ መጀመሩን ተከትሎ፣ በአየር ንበረት ለውጥ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የሚጠይቁ ተቃዋሚዎች በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ጎዳናዎች ላይ ጥያቄ ሲያቀርቡ

የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ በኬንያ በመካሄድ ላይ ባለው የመጀመሪያው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ 4.5 ቢሊዮን ዶላር ለንጹህ ሃይል መዋዕለ ነዋይ እንደምትመድብ ቃል ገብታለች፡፡

ትናንት ሰኞ በኬንያ በተጀመረው ጉባኤ ተሳታፊ የሆኑ የሀገራት መሪዎች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የአየር ንብረት ለውጥ በአህጉሪቱ እያደረሰ ያለው ድርቅ እና ጎርፍ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ማፈናቀሉን፣ ድህነትንና ረሃብን ማባባሱን ተናግረዋል፡፡ ይህን አስከፊ ጉዳት ለመዋጋት የሚያስችል ጠንካራ ድምጽ እና ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ቀውሱ ዕድሎችንም የፈጠረ መሆኑን የተናገሩት የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ በችግር ላይ ያተኮሩ ውይይቶች ወደ መፍትሄ ተኮር እርምጃዎች እንዲሸጋገሩ ጠይቀዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ፣ አፍሪካ ለየአየር ንብረት ለውጥ መከሰት ያላት አስተዋጽኦ አነስተኛ ቢሆንም፣ ከበለጸጉ አገሮች አንጻር ያልተመጣጠነ ተፅዕኖ እንደሚደርስባት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋች ተቃዋሚዎች በበኩላቸው ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG