በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእስራኤል እርስ በርስ የተጋጩ ኤርትራውያን ከሀገር መባረር እንደሚጠብቃቸው ተገለጸ


በእስራኤል እርስ በርስ የተጋጩ ኤርትራውያን ከሀገር መባረር እንደሚጠብቃቸው ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:20 0:00

በኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች እና በተቃዋሚዎች መካከል፣ በሳምንቱ መጨረሻ፣ በቴል አቪቭ - እስራኤል በተፈጠረ ግጭት፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መጎዳታቸውንና ንብረትም መውደሙን ተከትሎ፣ የአገሪቱ ባለሥልጣናት፣ በግጭቱ የተሳተፉ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎችን ከሀገር እንደሚያስወጧቸው እየዛቱ ናቸው።

የኤርትራን 30ኛ የነፃነት ቀን አስመልክቶ፣ ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ፣ በቴል አቪቭ ተዘጋጅቶ በነበረ ክብረ በዓል ላይ፣ የኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች በአንድ ወገንና ተቃዋሚዎች በሌላ ወገን ተሰልፈው በተፈጠረ ኀይል የተቀላቀለበት ግጭት ዐያሌዎች ተጎድተዋል። የፖሊስ አባላትም ጉዳት እንደደረሰባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በበኩላቸው፣ የኤርትራን ስም ለማጠልሸት ይሻሉ ያሏቸው ኀይሎች፣ በሁከት እና ንብረት በማውደም ሕጋዊውን ክብረ በዓል ለማስተጓጎል ሞክረዋል፤ ብለዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG