በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን ከፍተኛ ጄኔራል በጦርነቱ ዙሪያ ለመነጋገር ደቡብ ሱዳን ገቡ


የሱዳን ጦር አዛዥ ጄኔራል አብዱል ፈታህ ቡርሃን
የሱዳን ጦር አዛዥ ጄኔራል አብዱል ፈታህ ቡርሃን

በሱዳን የሚካሄደው ጦርነት በሚያዚያ ወር ከጀመረ ወዲህ ሁለተኛ የውጪ ጉዟቸውን እያካሄዱ ያሉት የሱዳን ከፍተኛ ጄኔራል ደቡብ ሱዳን ገቡ።

የገዢው ሉዓላዊ ምክርቤት ሊቀመንበር የሆኑት ጄኔራል አብዱል ፈታህ ቡርሃን በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ የሚገኘው አየር ማረፊያ ሲደርሱ በፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር አቀባበል ከተደረገላቸው በኃላ በሱዳን ስላለው ግጭት ወደሚወያዩበት ስፍራ ማምራታቸውን ምክርቤቱ አስታውቋል።

ቡርሃን ወደ ጁባ ባደረጉት ጉዞ፣ ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው አሊ አል-ሳዲቅ፣ የደህንነት ባለስልጣን ሀላፊ ጄኔራል አህመድ ኢብራሂም ሙፋዴል እና ሌሎች ወታደራዊ ባለስልጣናት አብረዋቸው እንደተጓዙ ተገልጿል።

በሱዳን የሚካሄደው ጦርነት ዋና ከተማዋን ካርቱምን ወደ የከተማ ጦር አውድማነት የቀየራት ሲሆን፣ ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች ከተማዋን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር አልቻሉም። እ.አ.አ ከ2ሺዎቹ መጀመሪያ አንስቶ የዘር ማጥፋት ዘመቻ እንደተካሄደበት በሚገልፅበት ምዕራብ ዳርፉር ክልልም እንዲሁ ግጭቱ ዘርን መሰረት ወዳደረገ ጥቃት አምርቶ፣ የፈጥኖ ደራሹ ኃይል እና አጋር የአረብ ሚሊሺያዎች የአፍርካ ዝርያ ያላቸውን ማህበረሰቦች ማጥቃታቸውን የመብት ተሟጋች ቡድኖች እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።

የደቡብ ሱዳን ካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ማርቲን ኤሊያ ሎሙሮ፣ የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት በሱዳን ያለውን ግጭት ለመፍታት መፍትሄ እንዳላቸው መናገራቸውን የፕሬዝዳንቱ ፅህፈት ቤት ያወጣው መግለጫ አስታውቋል።

"ፕሬዝዳንት ኪር ለሱዳን ቅርበት እና እውቀት ያላቸው ብቸኛ ሰው መሆናቸው ይታወቃል፣ እናም ለሱዳን ቀውስ መፍትሄ ሊያገኙ ይችላሉ" ሲሉ ሎሙሮ መናገራቸውን መግለጫው አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG