በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያና የቱርክ መሪዎች በዩክሬን እህል ስምምነት ዙሪያ ተወያዩ


የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቱርክ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶዋን ጋር በሶቺ፣ ሩሲያ ስብሰባ አካሂደዋል - ነሐሴ 29፣ 2015
የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቱርክ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶዋን ጋር በሶቺ፣ ሩሲያ ስብሰባ አካሂደዋል - ነሐሴ 29፣ 2015

ዩክሬን የእህል ምርቶቿን ወደውጪ ለመላክ የሚያችላትን ስምምነት ለማደስ ቱርክ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥረት እያደረጉ ባሉበት ወቅት፣ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን ጋር ተወያይተዋል።

"የእህል ስምምነቱን ጉዳይ ልታነሳ እንዳሰብክ አውቃለሁ" በማለት ውይይታቸውን የጀመሩት የሩሲያ ፕሬዝዳንት "በዚህ ጥቃቄ ዙሪያ ለመደራደር በራችን ክፍት ነው" ብለዋል።

ኤርዶዋን በበኩላቸው በስብሰባው ማጠናቀቂያ "ለዓለም፣ በተለይ ደግሞ ለታዳጊ የአፍሪካ ሀገራት፣ ጠቃሚ የሆነ እርምጃ ይሆናል" የሚል መልዕክት እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።

መሪዎቹ ሶውቺ በተሰኘው የሩሲያ ከተማ ውይይታቸውን ያካሄዱት፣ የሩሲያ እና የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባለፈው ሳምንት ከተነጋገሩ በኃላ ሲሆን፣ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ከውይይቱ በኃላ በሰጡት መግለጫ፣ የጥቁር ባህል እህል እንቅስቃሴን በድጋሚ ለመጀመር ሩሲያ እንዲሟሉላት የምትፈልገውን ዝርዝር ለቱርክ መስጠታቸውን ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የሩሲያ ጦር ከጥቁር ባህር በስተሰሜን ምዕራብ አራት ከፍተኛ ፍጥነት ያላቸው የዩክሬን ወታደራዊ ጀልባዎችን እንዳወደመ፣ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ሰኞ አስታውቋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቴሌግራም በኩል ባወጣው መልዕክት፣ ጀልባዎቹ የዩክሬንን ወታደሮች ጭነው ወደ ክሬሚያ የባህር ዳርቻ እያመሩ ነበር ብሏል።

የዩክሬን አየር ኃይል በበኩሉ፣ ምሽቱን የሩሲያ ድሮኖች፣ ላለፉት ጥቂት ወራት እህል ወደ ውጪ ለመላቅ ቁልፍ ቦታ ሆኖ ያገለገለውን እና በዳንዩብ ወንዝ አቅራቢያ የሚገኘውን ኢዝማኤል አካባቢን ጨምሮ፣ ወደተለያዩ የዩክሬን ክፍሎች እንደሚያመሩ በመግለፅ በርካታ ማስጠንቀቂያዎችን አውጥቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG