በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ አፍሪካ ለሩሲያ የጦር መሳሪያ እንደሸጠች የሚያሳይ ማስረጃ አልተገኘም - ራማፎሳ


ፋይል - የደቡብ አፍርካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ
ፋይል - የደቡብ አፍርካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ

የሩሲያ መርከብ፣ ለሩሲያ ጥቅም የሚውል የጦር መሳሪያ ከደቡብ አፍሪካ መውሰዱን የሚያሳይ ምንም ማስረጃ አለመኖሩን፣ ጉዳዩን ሲያጣራ የቆየው ገለልተኛ ቡድን ማረጋገጡን የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት እሁድ እለት አስታወቁ።

በደቡብ አፍሪካ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የሆኑት ሩበን ብሪጌቲ በግንቦት ወር ላይ፣ የሩሲያ መርከብ፣ ወደ ሩሲያ የሚጓጓዙ የጦር መሳሪያዎች ጭነት ለመቀበል ኬፕ ታውን አቅራቢያ በሚገኘው ሲሞን ታውን የተሰኘ የባህር ኃይል ጣቢያ ቆሞ ነበር ሲሉ ክስ አቅርበው ነበር።

"ለሩሲያ የጦር መሳሪያ አቅርቦትን በተመለከተ የተነሱት ክሶች አንዳቸውም እውነት መሆናቸው አልተረጋገጠም" ያሉት ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ "የጦር መሳሪያ ወደ ውጪ ለመላክ ፈቃድ አልተሰጠም፣ የጦር መሳሪያ ወደ ውጪ አልተላከም" ብለዋል።

ደቡብ አፍሪካ ቀርቦባት የነበረው ክስ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያደረገችውን ወረራ በተመለከተ ያላትን ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ ከቶት የነበረ ሲሆን ከምዕራቡ ዓለም ሊጣልባት ለሚችል ማዕቀብም አጋልጧት ነበር።

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ክሱ የሀገሪቱን ገፅታ "አበላሽቷል" ሲሉ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG