በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጋቦን መፈንቅለ መንግስት መሪ ለምርጫ እንደማይቸኩሉ አስታወቁ


በዚህ ሳምንት የጋቦን ፕሬዚደንት አሊ ቦንጎን ከስልጣን ያስወገደው መፈንቅለ መንግስት መሪ ያለፉ ምርጫዎችን ስህተት ላለመድገም ለምርጫ መቸኮል እንደማያስፈልግ ተናግረዋል።
በዚህ ሳምንት የጋቦን ፕሬዚደንት አሊ ቦንጎን ከስልጣን ያስወገደው መፈንቅለ መንግስት መሪ ያለፉ ምርጫዎችን ስህተት ላለመድገም ለምርጫ መቸኮል እንደማያስፈልግ ተናግረዋል።

በዚህ ሳምንት የጋቦን ፕሬዚደንት አሊ ቦንጎን ከስልጣን ያስወገደው መፈንቅለ መንግስት መሪ ያለፉ ምርጫዎችን ስህተት ላለመድገም ለምርጫ መጣደፍ እንደማያስፈልግ ተናገሩ ። የእሳቸው ንግግር የተሰማው ወታደራዊው መኮንኖች ቡድን(ሁንታ) ስልጣን ለሲቪል አስተዳደር እንዲመልስ ጫና እየበረታ ባለበት ወቅት ነው።

አሊ ቦንጎ ለሶስተኛ ጊዜ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸው በታወጀ ከደቂቃዎች በኃላ ነበር በጄኔራል ብሪስ ኦሊጊ ንጌማ የተመሩት ወታደራዊ መኮንኖች ረቡዕ ዕለት መንበረ ስልጣኑን የተቆጣጠሩ።

መኮንኖቹ ቦንጎን በቁም እስር ላይ በማዋል ፣ ጄኔራል ንጌማን ርዕሰ ሀገር አድርገው በመሾም የቦንጎ ቤተሰብን የ56 አመታት የስልጣን ዓመታት ቋጭተዋል ።

የጋቦን መፈንቅለ መንግስት በምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ ቀጠና በሦስት ዓመታት ውስጥ የተፈጸመ ስምንተኛ መፈንቅለ መንግስት ሲሆን ፣ በዋና ከተማይቱ ሊብሬቪል በርካቶች በድጋፍ ደስታቸውን ለመግለጽ ወደ አውራጎዳናዎች ወጥተዋል። ። ይሁንና ከውስጥ እና ከውጭ ሀገራት ውግዘትንም ቀስቅሷል ።

ጄኔራል ንጌማ አርብ ማምሻውን በቴሌቭዥን ቀርበው ባደረጉት ንግግር ወታደራዊው አስተዳደር በፍጥነት እና እርግጠኝነት ስራውን መከወን እንደሚቀጥል ነገር ግን ተመሳሳይ ሰዎችን በስልጣን ላይ በማቆየት “ተመሳሳይ ስህተቶችን የሚደጋገሙ” ምርጫዎች ሁንታው እንደሚያስወግድ ተናግረዋል።

የመካከለኛው አፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢሲሲኤስ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በአፍሪካ ህብረት የሚመሩ አጋሮች ፣ ሀገሪቱ በፍጥነት ወደ ህገ-መንግስታዊ ስርዓት እንድትመለስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ማሳሰቡን ሀሙስ ዕለት ባደረገው ድንገተኛ ስብሰባው ላይ አስታውቋል።ጥሪውን ሰኞ ዕለት መልሶ እንደሚያሰማም ይጠበቃል።

የቅዳሜው ምርጫ ትክክለኛ አሸናፊ ነኝ ያለው የጋቦኑ ዋና ተቃዋሚ ቡድን አልተርናንስ 2023፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ወታደራዊ መኮንኖቹ ስልጣን ለሲቪሎች እንዲመልሱ እንዲያበረታታ አርብ ዕለት አሳስቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG