በቱርክ ኢስታንቡል ከተማ፣ በጠባቡ የቦስፈረስ የባሕር ወሽመጥ በኩል የሚያልፉ መርከቦችን፣ አንድ ሰው በፎቶ ካሜራቸው መከታተል ይዘዋል፡፡ ነገርዬው፣ የጊዜ ማሳለፊያ እንዲኾናቸው በግላቸው የጀመሩት ነው። ታዲያ በክትትላቸው፣ ሩስያ በወረራ በያዘቻቸው የዩክሬን ወደቦች በኩል የተጣሉባትን ማዕቀቦች ተላልፋ የምትልካቸውን የጭነት መርከቦች ሲመለከቱ፣ መረጃውን በካሜራቸው እያስቀሩ ይሰበስባሉ።
ከዚኹ የአንድ ግለሰብ የግል ተነሣሽነት፣ ዓለም አቀፍ ብዙኀን መገናኛዎች እና ሩስያ ማዕቀቦቹን ማክበሯን የሚከታተሉ ሌሎችም ድርጅቶች፣ እጅግ ጠቃሚ መረጃ እያገኙ ናቸው።
ዶሪያን ጆንስ ከኢስታንቡል ያጠናቀረው ዘገባ ፣ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም