በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዐዲሶች ክልሎች ያለምርጫቸው የተደለደሉ ሠራተኞች ቅሬታቸው እንዳልታየላቸው ገለጹ


በዐዲሶች ክልሎች ያለምርጫቸው የተደለደሉ ሠራተኞች ቅሬታቸው እንዳልታየላቸው ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:08 0:00

በዐዲሶች ክልሎች ያለምርጫቸው የተደለደሉ ሠራተኞች ቅሬታቸው እንዳልታየላቸው ገለጹ

በቅርቡ ወደ ሁለት የተለያዩ ክልሎች የተከፋፈለው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የቀድሞው ሠራተኞች፣ በየክልሎቹ የተደለደሉበት አሠራር፣ በምርጫቸው ላይ የተመሠረተ እንዳልኾነ ያቀረቡት ቅሬታ እንዳልታየላቸው ተናገሩ።

በሺሕዎች የሚቆጠሩት ሠራተኞቹ፣ ወደየምድብ ክልሎቻቸው ለመጓዝ ዝግጅቱም ፍላጎቱም እንደሌላቸው ገልጸው፣ ለአቀረቡት ቅሬታ ምላሽ እየተጠባበቁ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡

በአንጻሩ፣ ዐዲሶቹ የደቡብ ኢትዮጵያ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች፣ ሠራተኞቻቸውን ወደየተመደቡበት የማጓጓዝ እና የማደራጀት ተግባራትን በቅርቡ እንደሚያጠናቀቁ አስታውቀዋል።

ከክልሎቹ ማደራጃ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። በጉዳዩ ላይ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር አቶ አድማሱ ዓለማየሁ፣ የድልድል ውሳኔው የሠራተኞችን መብት የጣሰ እንደኾነ ተችተዋል፡፡ ችግራቸው፣ በቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ታይቶ ምላሽ ካልተሰጣቸው፣ ወደ ፍርድ ቤት መውሰድ እንደሚችሉ አመልክተዋል። ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG