በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ የ'ፕራውድ ቦይስ' መሪ 17 ዓመት ተፈረደበት


ፋይል - በስተቀኝ የሚታየው ጆሴፍ ቢግስ ከሌሎች የፕራውድ ቦይስ አባላት ጋር ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ምክርቤት ሲያመሩ
ጥር. 6, 2021.
ፋይል - በስተቀኝ የሚታየው ጆሴፍ ቢግስ ከሌሎች የፕራውድ ቦይስ አባላት ጋር ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ምክርቤት ሲያመሩ ጥር. 6, 2021.

የዩናይትድ ስቴትስ የፌደራል ፍርድ ቤት ዳኛ፣ 'ፕራውድ ቦይስ' የተባለው የቀኝ አካራሪዎች ቡድን መሪ ጆሴፍ ቢግስን የ17 ዓመት እስር ፈርደውበታል።

ጆሴፍ የተፈረደበት፣ ከህዝብ የተውጣጡ ዳኞች፣ እ.አ.አ በ2020 ፕሬዚዳንት ትራምፕ የተሸነፉበትን የምርጫ ውጤት ለመቀልበስ በማሴርና፣ ጥር 6 በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ህንጻ ላይ በተነሳው አመጽ በነበረው ሚና ጥፋተኛ ነው በማለቱ ነው።

በፌደራል ዳኛው ቲሞቲ ኬሊ የተሰጠው የእስር ቅጣት፣ ዐቃቢ ህጉ ከጠየቁት የ33 ዓመት የእስር ጊዜ በጣም ያነሰ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የቅጣት ውሳኔው ከመተላለፉ በፊት ቢግስ ስለ ድርጊቱ ይቅርታ ጠይቋል፡፡

የወሲብ ጥቃት የደረሰባት ሴት ልጁ የሱን እርዳታ እንደምትጠባበቅ ሲቃ እየተናነነቀው በመግለጽ ቅጣቱ እንዲቀልለት ዳኛውን የተማጸነ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ሌሎች የፕራውድ ቦይ መሪዎችም ቅጣታቸውን እየተጠባበቁ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG