በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኡበር በኬንያ የኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌት አገልግሎት ጀመረ


ኡበር በኬንያ የኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌት አገልግሎት ጀመረ
ኡበር በኬንያ የኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌት አገልግሎት ጀመረ

የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭው ኡበር ኬንያ ውስጥ የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ትናንት ሐሙስ አስታወቀ።

አገልግሎቱ በአፍሪካ የመጀመሪያው መሆኑን የገለጸው ኡበር፣ እ.አ.አ በ2040 በዓለም ከልቀት ነጻ የሆነ አገልግሎት የመሰጠት ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል።

የኡበር ከኬንያ በተጨማሪ፣ ከሰሃራ በታች ባሉ እንደ ናይጄሪያ፣ አይቮሪኮስት፣ ጋና፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛንያና ደቡብ አፍሪካ የመሳሰሉ ሀገራት ሌሎች ገበያዎች እንዳሉት ሮይተርስ ዘግቧል።

አረንጓዴውን የኡበር አገልግሎት የሚጠቀሙ አሸከርካሪዎች ከ30 እስከ 35 ከመቶ የሚሆን ወጭ እንደሚቀንስላቸው ዘገባው አመልከቷል፡፡

ባለፈው ወር፣ የኬንያውፕሬዚዳንትዊሊያም ሩቶ፣ የመንገድ ላይ የኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌቶች ቁጥር በ 2024 መጨረሻ ላይ አሁን ካለው 2,000 ወደ 200,000 አድጎ ማየት እፈልጋለሁ ብለው መናገራቸውም በዘገባው ተጠቅሷል ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG