በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰዎች ህይወት የጠፋበት ህገወጡ የጆሃንስበርግ ህንጻ እያነጋገረ ነው


በጆሃንስበር የደረሰው አስከፊ የእሳት ቃጠሎ
በጆሃንስበር የደረሰው አስከፊ የእሳት ቃጠሎ

በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ 12 ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 74 ሰዎችን መግደሉ በተነገረለት የሐሙሱ እሳት ቃጠሎ፣ የሞቱ የሰዎችን አስክሬን አሳሽ ውሾች እያፈላለጉ መሆኑ ተነገረ።

200 ሰዎች ይኖሩበት ነበር በተባለው ባለ አምስት ፎቅ ህገ ወጥ ህንጻ ላይ በደረሰ ቃጠሎ ከ50 በላይ ሰዎች መጎዳታቸው ተዘግቧል። ባለሥልጣናት ሰዎች ወደ ስዌቶ አስክሬን ማቆያ በመሄድ ቤተሰቦቻቸውን እንዲለዩ መጠየቃቸውም ተገልጿል፡፡

አደጋው የደረሰበት ህንጻ ህገ ወጥነት አነጋጋሪ ሲሆን ደቡብ አፍሪካ መኖሪያ ቤትን አስመልክቶ ያለችበትን ቀውስ ያሳያል ተብሏል፡፡

“በመካከለኛው የከተማው ክፍሎች ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግርን አስመልክቶ አንድ ነገር እንድንጀምር የማንቂያ ደወል ነው” ሲሉ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራሞፎሳ ተናግረዋል፡፡

ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍል አባላት በሚኖሩበት ህንጻ በሌሊት ከተነሳው እሳት ለማምለጥ በአደጋ ግዜ መውጪያው በኩል ለመውጣት የሞከሩት ነዋሪዎች በሩ ባለመከፈቱ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

የአደጋ ግዜ ሠራተኞች በሩን በከፈቱበት ወቅት በርካታ አስከሬኖች በበሩ አቅራቢያ ተከማችቶ ማግኘታቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG