በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ለታይዋን ወታደራዊ ዕርዳታ አጸደቁ


ለታይዋን ወታደራዊ ዕርዳታ ፀደቀ
ለታይዋን ወታደራዊ ዕርዳታ ፀደቀ

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አስተዳደር፣ በተለምዶ ሉአላዊ ሀገሮች የሚሰጥ ወታደራዊ ዕርዳታ ለታይዋን እንዲሰጥ ትናንት ወስኗል። ውሳኔው ለተወካዮች ምክር ቤት መላኩንም የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።

ሮይተርስ ተመልክቼዋለሁ ያለውና ለኮንግረስ የተላከው ማስታወሻ፣ የሀግሪቱ የውጪ ጉዳይ መስሪያቤት 80 ሚሊዮን ዶላር ወታደራዊ ዕርዳታ ለታይዋን እንደሚሰጥ አመልክቷል።

ገንዘቡ የታዋንን የመከላከል ብቃት ለማሳደግ፣ የባህር ኃይል ደህንነቷን ለማጠናከር እና ለሌሎችም ወታደራዊ ተግባራት እንደሚውል ተጠቁሟል።

የተወካዮች ም/ቤቱ የሪፐብሊካን ፓርቲ የውጪ ጉዳይ ኩሚቴ ሊቀ መንበር የሆኑት ማይክል ማኮል እንዳሉት፣ የባይደን አስተዳደር “በስተመጨረሻ” ለታይዋን ዕርዳታ በማድረጉ ደስተኛ ነኝ ብለዋል።

ዕርዳታው ታይዋን በቀጠናው ዲሞክራሲያዊ ኃይሎችን ለመጠበቅ የምታደርገውን ጥረት በማገዝ ረገድ ብቻ ሳይሆን፣ ጠብ ጫሪ ካሉት የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የሚመጣን ስጋት በመከላከል፣ ብሔራዊ ደህንነትን ለማስጠበቅ ይረዳል ሲሉ ማኮል በመግለጫቸው አመልክተዋል።

ታይዋንን እንደ ግዛቷ የምትቆጥረው ቤጂንግ፣ ዋሽንግተን ከዴሴቲቱ ጋር ኦፊሴላዊ ግንኙነት እንዳታደርግ ስታስጠነቅቅ ቆይታለች፡፡ አሜሪካ ከታይዋን ጋር ያላትን ማንኛውንም ወታደራዊ ግንኙነት እንድታቆምም ስትጠይቅ ቆይታለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG